Fana: At a Speed of Life!

ህጋዊ የሰውና የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የዜጎች መብትና ጥቅም ለማስከበር ህጋዊ የሰውና የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር በባህሬን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ገለጹ፡፡

በባህሬን አዲሱን ዓመት እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ አስመልክቶ በዕለቱ የባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ዲፐሎማቶችና ሰራተኞች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ የኮሚኒቲ አደራጅ ኮሚቴዎች፣ በባህሬን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት ተከበሯል፡፡

በባህሬን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በወቅቱ ባደረጉት ንግግር÷ በባህሬን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በባህሬን የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እያደረጉ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

ይህንኑ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

አያይዘውም ሁሉም የሃገሩ አምባሳደር በመሆን የኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ እንዲሁም የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር ህጋዊ የሰውና የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በህገ-ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር የሚሳተፉ ሰዎችን ሁሉም ተባብሮ ለህግ ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

እለቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ‘የኛ የኢትዮጵያዊያን የሉዓላዊነት መገለጫ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ በይቻላል መንፈስ ‘እንደጀመርን እንጨርሰዋለን!’ በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

በእለቱም ከ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጽሟል፡፡

ተሳታፊዎቹም የህዳሴ ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲሁም መንግስት የያዛቸውን ዘርፈ ብዙ ግቦች እንዲሳካ የድርሻቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.