Fana: At a Speed of Life!

በአቶ መላኩ አለበል የተመራው የባለሀብቶች ቡድን በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የተመራው የባለሀብቶች ቡድን በሰሜን ጎንደር ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ለመከላከያ ሰራዊት እና ለአማራ ልዩ ሀይል ድጋፍ አድርጓል።
በሽብር ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸውየህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ፥ ለደባርቅ ዳባትና የአካባቢው ህዝቦች የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ላበረከቱት አስተዋዕፆ አቶ መላኩ በልዑኩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በጦርነቱ ወቅትም የደረሱ ጉዳቶች ከጦርነት ቀጠናው በመጡ ሰዎች አንደበት የቀረበ ሲሆን፥ ንፁሃንን በጅምላ ጨፍጭፈው መሄዳቸውን ተናግረዋል።
በጭና ከተሰው ንፁሃን በተጨማሪ ከ100 በላይ ቤቶችም ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው ከጭፍ ጨፋው የተረፉ ንፁሃን መጠለያ አልባ መሆናቸውም በተጎጂዎቹ ቀርቧል።
በአፄ ይስሃቅ ዘመነ መንግስት የተገነባው የአካባቢው ጭና ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያንን በምሽግነት ሲጠቀሙበት ከቆዩ በኋላ በቅርስ ጥበቃ ተቋም በቅርስነት የተመዘገቡ ንዋየ ቅድሳት የብርና የነሀስ መስቀል፣ የብራና መፃህፍቶችም መመዝበራቸውን ቀሳውስቱ ገልፀዋል።
እስካሁን በአካባቢው ከ200 በላይ ንፁሀን የተገደሉ ሲሆን፥ ከ120 በላይ ሰዎች እንደጠፉ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
በደባርቅ ዞን ቦዛ አብርሀም ቀበሌ ከ 15 ሺህ በላይ የሚሆነው ነዋሪው የህብረተሰብ ክፍልም በሽብር ቡድን በደረሰበት ዘረፋ ለችግር እንደተጋለጠ እና መጠለያ አልባ እንደሆነም ከአካባቢው የመጡ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ነዋሪዎቹ በደረሰባቸው ጉዳት ለችግር እንደተጋለጡ ገልፀው ፥ ንብረታቸውና አዝመራቸው በመውደሙ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
ከባለሀብቶችም አቶ በላይነህ ክንዴ እና ሌሎች ታዋቂ ባለሀብቶች የተገኙ ሲሆን፥ እኛ በቦታው የተገኘነው ለተጎናፀፋችሁት ድል ለማመሰግን እና ሀገር ለመጠበቅ በከፈላችሁት መስዋትነት እኛ በሰላም እየኖርን በመሆኑ የደረሰባችሁን ችግር ደግሞ ለመካፈል ነው ብለዋል።
የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ሰኢድ ትኩ የ መከላከያው እና የአካባቢው ህብረተሰብ እንዲሁም አመራሮች በጋራ በወሰዱት እርምጃ የጠላት ፍላጎት ዳግም እንዳያንሰራራ ሆኖ ተመቶ ከሽፏል ብለዋል።
ጀነራሉ ሙሉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ለመከላከያው የሚያደርገው ድጋፍ በአንድ ቋት ይሰብሰብ እንጅ ግንባር ድረስ ላለው የሰራዊቱ አባል እየደረሰ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ያሉ ሲሆን ለዚህም በዕዛቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አቶ ፈንታ ደጀን የኢፌድሪ ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታ ፥ጠላት ላይ እየተወሰደ ያለው ጥቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነገር ግን አሁንም ጠላት ሙሉ ለሙሉ እስኪደመሰስ ድረስ በተገኘው ጊዚያዊ ድል ተዘናግተን ዳግም እንዲደራጅ ጊዜ ልንሰጠው አይገባም ተከታትለን ግብዐተ መሬቱን ልናፈጥነው ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያላለም ፈንታሁን ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ፥ የዞኑ ህዝብ የሽብር ቡድኑን የመደምሰስ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ገልጸዋል ።
በኤልያስ አንሙት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
164
People Reached
439
Engagements
Boost Post
410
6 Comments
18 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.