Fana: At a Speed of Life!

 በቀን አንድ እንቁላል መመገብ ለልብ ጤንነት ጠቃሚ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀን አንድ እንቁላል መመገብ ለልብ ጤንነት ጠቃሚ መሆኑን በአሜሪካ የተደረገ አንድ ጥናት ተጠቆመ፡፡

እንቁላል ብዙ ጠቃሚ ቫይታሚኖች ፣ ማዕድናት እና እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን  በውስጡ ይዟል፡፡

የእንቁላል ነጭ ክፍል በአብዛኛው ፕሮቲን የያዘ ሲሆን  አስኳሉ ደግሞ ብረት ፣ ፎስፈረስ ፣ ቫይታሚን ዲ ፣ ቢ ቪታሚኖችን ፣ ጤናማ ስብን እና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንም ያካተተ በመሆኑ ለጤና ጠቃሚ ነው ተብሏል ፡፡

እንቁላል በርካታ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ መያዙን የሚገልጹት ተመራማሪዎቹ  የልብ ህመም  ወይም የስኳር ህመም  ያለባቸው ሰዎች እንቁላል ቢመገቡ ጤናቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሌለ ነው የተነገረው።

በጥናቱ እንደተጠቆመው በእንቁላል እና በደም ኮሌስትሮል ፣ በእንቁላሉ ይዘትና ሌሎች በሽታ አጋላጭ በሆኑ መንስኤዎች መካከል ምንም  አይነት ግንኙነት እንዳልተገኘ ጥናቱ አመላክቷል፡፡

እነዚህ ውጤቶች ለጤነኛ ግለሰቦችም ሆነ  የደም ቧንቧ ህመም ላለባቸው ሰዎች በሰፊው የሚተገበሩ  ናቸውም ተብሏል ፡፡

ጥናቱ በሶስት ቡድኖች ተከፍሎ በ6 አህጉራት በ50 ሀገራት ውስጥ በሚኖሩ የተለያየ የገቢ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ያሳተፈ መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚህም በርካቶቹ በቀን ውስጥ አንድ ወይንም ከአንድ ያነሰ እንቁላል የተጠቀሙ ሲሆን በውጤቱም ጤናማ እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል።

ከ177 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ የተገኘ መረጃዎች የተተነተኑበት በመሆኑ ውጤቶቹ በሰፊው የሚተገበሩ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

እንቁላሎች ጠቃሚ ለሆኑ ንጥረ ነገሮች ምንጭ ቢሆኑም አንዳንድ የአመጋገብ መመሪያዎች እንቁላል የሰዎችን በልብ በሽታ የመያዝ እድልን ይጨምራሉ በሚል ስጋት በሳምንት ከሶስት እንቁላሎች በታች መመገብ እንዳለባቸው ይመክራሉ።

ይህ አስተያየት ለረጅም ጊዜያት ሲሰጥ የነበረው  እንቁላል ለልብ በሽታ ያገልጣል ከሚል ስጋት የተነሳ ነበር።

ሆኖም ከዚህ ቀድም እንቁላል እና ጤናን በተመለከተ የተካሄዱት ጥናቶች  የሚጋጩ ግኝቶችን በማስገኘታቸው መሆኑን የጥናቱ ዋና ተመራማሪ ሳሊም ዩሱፍ  ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-www.upi.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.