Fana: At a Speed of Life!

በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ከ201 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት ተፈፅሟል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ለ2014 የዘመን መለወጫ በዓል ከ201 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የህብረት ስራ ማህበራቱ በክልሎች ከሚገኙ የግብርናና የኢንዱስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው ቀጥታ የገበያ ትስሰር ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያቀርቡ መደረጉን የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ጌታቸው ገልጸዋል ።

በዚህም 95 ሚሊየን ብር የሚሆን የግብርና ምርቶች ፣ 9 ሚሊየን የእንሰሳትና የእንሰሳት ተዋጽኦ ውጤቶች እና 97 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ደግሞ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ቀጥታ የገበያ ትስስር በመፍጠር የዋጋ ንረትን በመቀነስ በማህበራቱ ለህብረተሰቡ ማቅረቡን ተናግረዋል ።

በቀጣይም የህብረት ስራ ማህበራቱን በክልሎች ከሚገኙ የግብርናና የኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት በዘላቂነት ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ጥላሁን መናገራቸውን ከአዲስ አበበሳ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.