Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዓመት የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን አልፈን አዲስ ታሪክ የምናስመዘግብበት ይሆናል – የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ፈተናዎች በገጠሟት ቁጥር እንደ ብረት ጠንክራ የምትወጣ በመሆኗ “አዲሱ ዓመት የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን አልፈን አዲስ ታሪክ የምናስመዘግብበት እንደሚሆን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ተናገሩ።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት አዲሱ ዓመት የአገራችንን ሰላምና አንድነት የበለጠ የምናጠናክርበትና ወደ አዲስ ምጽራፍ የምንሻገርበት ይሆናል።
አክለውም ኢትዮጵያ የቀደምት አባቶችንን አኩሪ ታሪክ ለመድገምና አዲስ ታሪክ ለመስራት ከምታካሂዳቸው እንቅስቃሴዎች አንዱ ማሳያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ነው ብለዋል።
“የአገራችን ሉዓላዊነትና ታሪክ ተጠብቆ እዚህ ሊደርስ የቻለው አያቶቻችንና አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነትና ባስመዘገቡት ድል መሆኑን ያመከቱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ አሁን ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለው መንገድ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን በማለፍ አዳዲስ ታሪኮችን ለመስራት እንደሚያስችላት ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን ለማፍረስና ሉዓላዊነቷን ለመዳፈር ሁሌም የውስጥ ሃይሎች እና ከጀርባ ሆነው ድጋፍ የሚሰጡ ውጫዊ ጠላቶችሲዘምቱባት መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያውያን የጋራ ችግሮችን በድል ለመወጣት በአንድነት በመቆመው ታላቅ ታሪክ ሲያስመዘግቡ መኖራቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን የሉዓላዊነቷን ጉዳይ በቀይ መስመር አስምራ እየተሻገረች መሆኑን ገልጸው፥ በአዲሱ ዓመትም ያጋጠሟትን ፈተናዎች በድል በመወጣት ወደ ልማትና ወደ ዘላቂ ሰላም እንድትሻገር አንጠራጠርም” ብለዋል።
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ወገኖች ኢትዮጵያን ወደ ልማት ለማሻገር ትልቅ ስራ እየሰሩ መሆኑን
ጠቁመው፤ የግንባታውን ደረጃ በማየታችንም ከሚሰማው የበለጠ የሚያኮራ ስራ መሆኑንም ነው የገለጹት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.