Fana: At a Speed of Life!

ለዲፕሎማቶች ስልጠና መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲፕሎማቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ስልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን÷በስልጠናው ዓለምአቀፋዊ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሁነቶችና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ይዘቶች እንደሚዳሰሱ ተገልጿል።

በሚኒስትር ማዕረግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራር አቶ አወሉ አብዲ ÷ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀደምት ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ ብቃት ያላቸውን መሪዎች ለማፍራት የትምህርትና የስልጠና ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ዲፕሎማቶች ለየትኛውም ጥሪ ሁሌም ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው ያሉት አቶ ደመቀ በለውጡ የተለያዩ ውጤቶች ቢመዘገቡም ተግዳሮቶችና ፈተናዎች መግጠማቸውን አንስተዋል።

ራስ ወዳድና ሰላም ጠል ቡድኖች ሀገርን የማተራመስ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል ይሄንን ለመቀልበስ ሀገር ወዳድነትና በጋራ መቆም ይጠይቃል ነው ያሉት።

ለተሻለ የለውጥ ጉዞ ምርጫውን ያሸነፈው መንግስትም ሀገርን ወደፊት የሚያራምድ ስራ ይጠይቀዋል፣ ተቋማትም ይሄንን በሚመጥን ለውጥ ውስጥ ሊሆኑ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥናት በማድረግ ወደ ትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ደመቀ ከቀደሙት ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በጎዎችን በማስቀጠልና አዳዲስ አሰራሮችን በመጨመር ዘመኑ የሚጠይቀውን ዲፕሎማሲ ለመገንባት ይሰራል ነው ያሉት።

በዚህ ለውጥ ሚሲዮኖች መፈተሻቸውን ውጤታማ ተደራሽና ስኬታማ መሆናቸውን የማጤን ስራም እንደሚሰራ ተናግረው የሚሲዮኖችን አሰራርና ስምሪትንም በአዲስ መልክ የማደራጀት ስራ ይሰራል ብለዋል።

በአፈወርቅ እያዩና በበርናባስ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.