Fana: At a Speed of Life!

የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን የጋራ የፀጥታ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በፀጥታ አካላት የተከናወኑ ተግባራትበቀጣይ የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ በማድረግ ሊደገም ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተናግረዋል፡፡
የአዲሱ ዓመት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም ሌሎች የደህንነትና ፀጥታ አካላት ጉልህ ድርሻ ነበራቸውም ነው ያሉት፡፡
በተለይ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን ሆኖ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የማይተካ ሚና በመጫወቱ የጋራ የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡
የዘመን መለወጫን ጨምሮ በመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል፣ የኢሬቻ በዓላትና ሌሎች ትላልቅ ህዝባዊና መንግስታዊ ዝግጅቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የመከላከያ ሪፐብሊካን ጋርድና ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት የጋራ የፀጥታ ዕቅድ በማውጣት ሲሰሩ ቆይተዋል መባሉን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.