Fana: At a Speed of Life!

የድሬደዋ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የ350 ሚሊየን ብር ውል ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግንባታው ለአስር ዓመታት የተጓተተውን የድሬደዋ ሪፈራል ሆስፒታል ለማጠናቀቅ የሚያስችል ሰነድ ተፈራርሟል።
ፊርማውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም እና የኤቢ ኮንስትራክሽን ተወካይ አቶ ኢዛና አከለው አኑረዋል።
ተደጋጋሚ የዋጋ ግሽበትና የሆስፒታሉ ባለቤትነትን ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የማዞር ሂደቶች ፕሮጀክቱን እንዲጓተት እዳረገው የተናገረው ኤቢ ኮንስትራክሽን፣ አሁን ላይ ግን በተቀመጠው ቀነ ገደብ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተወካዩ ተናግረዋል።
ሆስፒታሉን በ2012 ዓ.ም ከከተማ አስተዳደሩ የተረከበው የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ፥ ላለፋት ሁለት ዓመታት የተለያዩ የሰነድ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዑባህ አደም በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በየዩኒቨርሲቲው ስር መተዳደሩ ለማህበረሰቡ ከሚሰጠው በዘለለ፣ ተማሪዎች ተግባር ተኮር ትምህርት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።
የድሬደዋ ሪፈራል ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ በአንድ ዓመት ተኩል ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
159
Engagements
Boost Post
153
6 Shares
Like

 

Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.