Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ ለጤና ተቋማትና ለህልውና ዘመቻ 120″ሚሊየን ብር የሚገመት መድሃኒት አቅርቧል

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የጎንደር ቅርንጫፍ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 120 ሚሊየን ብር የሚገመት መድሃኒት ለህልውና ዘመቻው በተለያዩ ግንባሮች ማቅረብ መቻሉን ገልፀ።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ አግማስ ተቋሙ የISO 9001/2015 አለምአቀፍ መስፈርትን አሟልቶ  ተሻላሚ መሆኑን ተከትሎ የተቋሙን አሰራር ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ተቋሙ ዘመናዊ አሰራር ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ብለዋል፡፡

ቅርንጫፉም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 120ሚሊየን ብር የሚገመት መድሃኒት ለህልውና ዘመቻው በተለያዩ ግንባሮች እንዲሁም ለጤና ተቋማት ማቅረብ መቻሉ የሚመሰገን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው የካይዘን አሰራር ሙሉ በሙሉ በመተግበር ውጤታማ መሆምኑ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የጎንደር ቅርንጫፍ ስራአስኪያጅ አቶ እንዳለው አስማማው በበኩላቸው÷ ዘመናዊ የተቋም አደረጃጀት እና የካይዘን አሰራር በቅርንጫፍ ተግባራዊ መደረጉ ተቋሙ ስራዎችን በቀላሉ ለመፈፀምና ተሸላሚ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.