Fana: At a Speed of Life!

የቡርጂ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 22 ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡርጂ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ግንባር ላይ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ለልዩ ሃይልና ለሚሊሻ አባላት ልዩ ልዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የልዩ ወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ማሬ አለማየሁ እንዳሉት፥ እስከ አሁን የልዩ ወረዳው ህዝብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
ነዋሪዎቹ 300 ኩንታል ጤፍ፣3 ሚሊን ብር ጥሬ ገንዘብ፣27 በግና ፍየል እንዲሁም ልዩ ልዩ ደረቅ ምግቦችን ድጋፍ አድርገዋል።
በዛሬው እለትም 22 ሰንጋዎችን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
በቀጣይም የልዩ ወረዳው ህዝብ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ሰንጋዎቹን ለደቡብ ክልል ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል ።
የክልሉ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መኮንን መኔቦ፥ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለሀገር መከላከያ የሚደረገው ልዩ ልዩ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው ፥ ህዝቡ የህልውና ማስከበር ዘመቻው በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
82
Engagements
Boost Post
74
1 Comment
7 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.