Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር አቶ አለምእሸት ተሾመ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ የገበያውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞቹን ከ200 በላይ ለማድረስ እየሰራ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በተለይ ዓለም አቀፋዊነቱን በሚያሳይ መልኩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ በትምህርት ዘርፍ የሚሰራቸው ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሀገራትን በእውቀት ለማስተሳሰር ጠቀሜታ ባለው የትምህርት ዲፕሎማሲ ከሶማሌላንድና ጀቡቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.