Fana: At a Speed of Life!

በ2014 የኢሬቻ በዓል አከባበርን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባ ገዳዎች በ2014 በሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ የኢሬቻን የተመለከተ ውይይት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም በፊንፊኔ እንዲሁም መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ እንደሚከበር ታውቋል።
የውይይት መድረኩን የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ከአባ ገዳዎች ሕብረት ጋር በመተባበር ነው የተዘጋጀው፡፡
በመድረኩ የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ÷ 2013 በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፈን ትልልቅ ድሎች ያስመዘገብንበት ወቅት ነበር ብለዋል፡፡
በ2014 ድሎቻችንን አጠናክረን በአሸናፊነት መንፈስ በርካታ ተግባራትን የምናከናውንበት ይሆናልም ነው ያሉት፡፡
የዘንድሮ የኢሬቻ በዓልም ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል።
በዓሉ የይቅርታ፣ የምስጋናና ኦሮሞዎች በአንድ ላይ ሆነው ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት መሆኑንም ተናግረዋል ።
“ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነት ምልክት መሆኑን ትውልዱ መገንዘብ አለበት” ሲሉም ነው ያስታወቁት።
የኢሬቻ በዓል ከዚህ ቀደም በተከበረበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በ2014 የበዓሉ አከባበር በሚያመላክት አቅጣጫ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በሙሉ ዋቅሹሜ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
55,690
People Reached
3,152
Engagements
Boost Post
611
87 Comments
13 Shares
Like

 

Comment
Share

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.