Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከግሪክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከግሪክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አምባሳደር ቴሜስቶክሊስ ዲሚትሪስ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በወቅቱም አምባሳደር ደሚቱ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የኢትዮ-ሱዳን የድንብር ጉዳይን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ቴሜስቶክሊስ ዲሚትሪስ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፥  በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት አውስተዋል።

አያይዘውም በሀገራቱ መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይታቸው መጨረሻም በሁለቱ አገራት መካከል ለረጀም ጊዜያት የዘለቀውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይመድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.