Fana: At a Speed of Life!

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረጉ ድጋፎችን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚሆኑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የምግብ እና ቁሳቁስ ግብአቶችን ለአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አስረከበ።
የአፋር ክልልን ከትግራይ ክልል ጋር በሚያዋስናቸው የተለያዩ የአፋር አካባቢዎች የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች ለተጠለሉ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲደረግ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር መሀመድ ኡስማን፥ ሠመራ ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ያደረገዉን ድጋፍ ጨምሮ እነዚህ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ያደረጉትን የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ለአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ማስረከባቸውን ከሰመራ ዩኒቨርስቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.