Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት በጀትና የስራ እቅድ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ብሄራዊ ኮሚቴ የፕሮጀክቱን የ2014 ዓ.ም በጀትና የስራ እቅድ አፀድቋል።

ብሄራዊ ኮሚቴው በፕሮጀክቱ ስር በዚህ አመት ሊሰሩ በታቀዱ ጉዳዮች ዙሪያም ውይይት አካሂዷል።

በፕሮጀክቱ ስር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱ  ሲሆን ፥ የስራ ዝርዝራቸውና በጀታቸው ቀርቦ ፀድቋል።

በዓመቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን ወደ መሬት የማውረድ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።

የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን ማስፋፋት፣ የህዝብ ተቋማት ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ዝርጋታ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ስራ፣ የግል የቴክኖሎጂ ተቋማትን አቅም መገንባት በስራው ውስጥ የተካተቱ  መሆናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.