Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴርና ፌዴራል ፖሊስ በኮቪድ 19 መመሪያዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴርና የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፌደራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት ምክትል ዘርፍ በጋራ በመተባበር ኮቪድ 19ን ለመከላከል ያለመ ውይይት አድርገዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ዲኤታዋ ሳህራላ አብዱላሂ ፥ በሀገራችን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እየከፋ ስለመጣ ጤና ሚኒስቴር ያስቀመጣቸውን ድንጋጌዎች ለማስፈፀም ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅርበት መመካከርና መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዲኤታዋ አክለውም፣ በሐይማኖታዊ በዓላት እና ሠላማዊ ሰልፎች በሚደረጉባቸው ማኅበራዊ አውዶች ውስጥ ኅብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዘናጋ በመምጣቱ ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት ምክትል ዘርፍ ኃላፊ፣ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ደረጄ ተካልኝ በበኩላቸው÷ ሠራዊቱ አመራሩና አባላት የኮቪድ 19 ቫይረስ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በጤና ሚኒስቴር የወጣውን መመሪያ ለማስፈፀም እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከጤና ሚኒስቴር መመሪያዎች መካከል የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ማድረግ፣ ርቀት መጠበቅ ፣ ከንኪኪ መራቅ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፥ አሁን ላይ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ በአቅርቢያቸው በሚገኙ የጤና ተቋማት በመሄድ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲከተቡ አስፈላጊው ሁሉ መመቻቸቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ መግለጻቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.