Fana: At a Speed of Life!

በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በነገሌ ከተማ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጂን ጉተማ ሳፋይ እንደገለጹት÷ ከትናንት በስቲያ በከተማው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽ ተገኝቷል።

ከተገኘው ካናቢስ ጋር ተያይዞ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

አደንዛዥ እጹ ከሻሸመኔ ከተማ ኩየራ አካባቢ ተጓጉዞ ለአሸባሪው ሸኔ እንዲደርስ የተዘጋጀ ስለመሆኑ አመላካች መረጃዎች መገኘታቸውን ዋና ሳጅን ጉተማ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.