Fana: At a Speed of Life!

ለህወሓትና ሸኔ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው-የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህወሓትና ሸኔ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ ፡፡
የጠቅላይ አቃቢ ህግ ቢሮ ሐላፊ አቶ አዩብ አህመድ ፥ ከፌደራል ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ፣ የመከላከያ ምስራቅ ዕዝ ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የክልሉ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ሽብረኞቹን ህወሓትና ሸኔን በገንዘብና በቁሳቁስ ይደግፋሉ የተባሉ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የተወሰኑት መለቀቃቸውና ሌሎች መረጃና ማስረጃ ተገኝቶባቸው ምርመራው ቀጥሏል ብለዋል፡፡
በዚህም 7 ድርጅቶች ታሽገው ምርምራ እየተደረገባቸው ሲሆን፥ 11 ተሸከርካሪዎች ደግሞ ስራ እንዲያቆሙ መደረጉን ገልጸዋል።
ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው የፀጥታ ሃይሉ በተለይም የመከላከያ ሰራዊቱ አካል የሆነው ምስራቅ ዕዝ መረጃ በመሰብሰብ ፣ በመተንተንና በማደራጀት እንዲሁም የሓይል ስምሪቱን በግንባር ቀደምትነት እየሰራ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
የህወሓትና የሸኔ የሽብር ሃይሎች በክልላችን የተደራጀ ወንጀል እና የሽብር ስራ እንዳይሰሩ ከመከላከል አንፃር መከላከያ ሰራዊቱ እያበረከተው ያለው የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ፣ ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጥምረትም ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው ነው ያሉት።
በቀጣይነትም ሽብርተኞችን በገንዘብም ይሁን በቁሳቁስ የሚደግፉ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, sitting and indoor
0
People Reached
79
Engagements
Distribution Score
Boost Post
74
3 Comments
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.