Fana: At a Speed of Life!

ወረዳው በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት የደረሰባቸውን ተማሪዎች በነፃ ተቀብሎ ለማስተማር ወሰነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትህነግ አሸባሪ ሃይል በፈጸመው ወረራና ጅምላ ጭፍጨፋ የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን በምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር ለአንድ ዓመት በነፃ ለማስተማር ወረዳው ወስኗል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን ዘውዴ ለፋና እንደገለጹት÷ አሸባሪው ቡድን በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከፈጸመው አሰቃቂ እልቂት፣ በተቋማት ላይ ያደረሰው ውድመት አሳዛኝ መሆኑን ነው ብለዋል።

በመሆኑም በወረዳው በሚገኙት 57 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአንድ ዓመት ለማስተማር የወረዳው ምክር ቤት ወስኗል።

የወረዳው አስተዳደር ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ለማስተማር የወሰነው በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን እንደሆነም ተጠቅሷል።

የመምረጫ መመዘኛውም ወራሪው ቡድን በፈጸመው ግፍ ምክንያት ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ትምህርት ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ ቤታቸው የፈረሰባቸውና በኑሮ የተቸገሩ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ወላጆቻቸው በግንባር ላይ ያሉ ህፃናት ተማሪዎችን እንደሆነም አስተዳዳሪው አብራርተዋል።
ተማሪዎቹ ተመርጠው እንዲላኩላቸውም ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና ለሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ በድብዳቤ ጠይቀዋል።

በተመስገን ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.