Fana: At a Speed of Life!

የቦርዱ አመራሮች መስከረም 20 ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት የመስክ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች መስከረም 20 ቀን 2014 ምርጫ በሚካሄድባቸውን አካባቢዎች የመስክ ጉብኝትና ውይይት አካሄዱ፡፡

በቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የተመራው ቡድን ከደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር፣ ከዞን አመራሮችንና በአካባቢው ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ጋር ምርጫውን በተመለከተ ምክክር አካሂዷል።

እንዲሁም ከድምጽ መስጫ ቀኑ በተጨማሪ በተመሳሳይ መስከረም 20 ለሚካሄደው ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ውይይት ተደርጓል።

በተመሳሳይ በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለና በቦርዱ አመራር አባል በሆኑት ብዙወርቅ ከተተ የተመራው ሁለተኛው ቡድን ከሐረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደርና በአካባቢው ላይ ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ጋር ተወያይቷል።

በጀጎል ልዩ ምርጫ ክልል እና በጀጎል ዙሪያ እና ሁንደኔ ምርጫ ክልል ያሉ መደበኛና ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመካሄድ ላይ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ ጎብኝቷል፤ የምርጫ አስፈጻሚዎችንና የዞን አስተባባሪዎችንም አነጋግረዋል።

በተጨማሪ የሐረሪና የድሬዳዋ የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ፣በድሬዳዋ ከተማ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸው ውስን የምርጫ ጣቢያዎችንም መጎብኘታቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቦርድ አመራር አባል ዶክተር አበራ ደገፋ እና ፍቅሬ ገብረሕይወት የተመራ ሶስተኛ ቡድን ደግሞ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳደርና በአካባቢው ላይ ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ጋር የተወያየ ሲሆን÷ በተጨማሪም በአካባቢው በመካሄድ ላይ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ በመጎብኘት የምርጫ አስፈጻሚዎችን እና የዞን አስተባባሪዎችን አነጋግሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.