Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች በሰሜን ወሎ ግንባር ለተሰለፈው የፀጥታ ሃይል ትኩስ ምግቦችን አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ 01 እና 02 ነዋሪዎች በሰሜን ወሎ ግንባር ለተሰለፈው የፀጥታ ሃይል ትኩስ ምግቦችን አቀረቡ።
በስፍራው የተገኙት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅፈት ቤት ሃላፊ አቶ ከድር እንድሪስ ፥ የከተማችን ማህበረሰብ በራሱ ተነሳሽነት በመደራጀት የሃገሩን ህልውና ለማስከበር ግንባር ላይ ላለው ሰራዊታችን ትኩስ ምግቦችን ሲያቀርብ ለ5ኛ ዙር ነው ብለዋል።
አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለመደምሰስ የህብረተሰቡ አብሮነት ከሰራዊቱ እንደማይለይ ሃላፊው ተናግረዋል።
ሰራዊቱን በመወከል ከህዝብ የተደረገለትን ድጋፍ የተረከቡት በግንባሩ የጦር አዛዥ በበኩላቸው፥ ሽብርተኛውንና ወራሪውን የጥፋት ሃይል ለመደምሰስ ህዝባችን እያደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ድላችንን የሚያፋጥንና የሰራዊቱን ስነ- ልቦና የሚገነባ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
1
Engagement
Boost Post
1
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.