Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከ800 ኪ.ሜ በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ለማከናወን አቅዷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን 244 ኪ.ሜ የሚደርስ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና 568 ኪ ሚ የሚሆን የመንገድ ጥገና ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሪፖርተር እንደነገሩት ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከመንገድ ፈንድ እና ከብድር የተገኘ 6 ቢሊየን ብር በጀት ተይዟል።

ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆን የአስፋልት መንገድ ግንባታ፣ ከ104 ኪ.ሜ በላይ የኮብልስቶን ግንባታ እንዲሁም 21 ነጥብ 12 ኪ.ሜ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚገነባ የአስፋልት መንገድ ይሰራል።

በሌላ በኩል 52 ኪ.ሜ የሚደርስ የጠጠር መንገድ ለመገንባት በእቅድ ተይዟል ።

46 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታም እንደሚካሄድ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ÷ በክረምት ወራት የተጎዱ 130 ኪ.ሜ የከተማ መንገዶች እና የሚሆን የአስፋልት የጥገና ስራ ይከናወናል ብለዋል።

50 ኪ.ሜ የኮብልስቶን እንዲሁም ከ79 ኪ.ሜ በላይ የጠጠር መንገድ ጥገና እንደሚከናወንም አስታውቀዋል።

በክረምት ወራት ለዋና መንገዶች መበላሽት ምክንያት የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች 317 ኪ.ሜ የሚደርስ ጥገና ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሆነም ነው የገለጹት።

በተጨማሪም 13 ሺህ የሚደርስ የመንገድ ላይ መብራት እና የአምፖል መቀየር ስራ በዋና መንገዶች ላይ እንደሚሰራም በበጀት ዓመቱ እቅድ ተካትቷል።

ባለፈው በጀት ዓመት የተጀመሩ የመንገድ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነም ታውቋል።

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.