Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቋረጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቋረጥ ለመቀነስ የሚያግዙ የሲስተም ማሻሻያዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ እያየሁ ሁንዴሳ እንደገለፁት፥ በጊቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የገዥ ሲስተም መቆጣጠሪያ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የሀገር አቀፍ ኃይል መቋረጥን መቀነስ ተችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም በአንድ ቦታ ላይ የሚከሰት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መቋረጥ ለሀገር አቀፍ የኃይል አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ይሆን ነበር ያሉት አቶ እያየሁ ፥ የኦፕሬሽን ሲስተሙን በማዘመን ችግሩን መቅረፍ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
የሀገር አቀፍ ኃይል መቋረጥ በተደጋጋሚ እንዳይከሰት ለማድረግ ሰፊ የሲስተም ማሻሻያዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ እያዩ ተናግረዋል፡፡
ስራ አስፈፃሚው እንደተናገሩት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን አጠቃላይ የኃይል ቁጥጥር ዑደት ለማዘመን ይረዳ ዘንድ ኮሪያ ፓወር ኮርፖሬሽን ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈፅሞ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡
በተጨማሪም የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ መቋረጥ በሚያጋጥምበት ወቅት ከሌሎች ጊዜያት በአጠረ ጊዜ ወደ ሥራ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
በጊቤ አንድ እየተስተዋለ ያለውን የመጠባበቂያ ዲዝል ጀነሬተር ችግር ለመቅረፍም የተሻለ አቅም ያለው ጀነሬተር መቅርቡንም ገልጸዋል።
በጊቤ አንድ እየተስተዋለ ያለውን የመጠባበቂያ ዲዝል ጀነሬተር ችግር ለመቅረፍም የተሻለ አቅም ያለው ጀነሬተር ማቅረብ መቻሉን የበለስ እና የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን የኦፕሬሽን ሲስተም ለማዘመንም በዘርፉ የካበተ ልምድ ካላቸው የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ጋር ውይይት መጀመሩን ሥራ አስፈፃሚ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.