Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የ2014 ዓ.ም ትምህርት ጥቅምት 1 ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ጥቅምት 1 ቀን 2014 እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ከትምህርት ቢሮው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው፥የ2014ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርትን ለማስጀመር መምህራን በየትምህርት ቤታቸው እስከ መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሪፖርት በማድረግ የመምህራን ጉባኤ ይደርጋል፡፡
በሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2014 ዓ.ም የትምህርት ሳምንት ከመስከረም 24 እስከ 28 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድም ገልጿል፡፡
የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 18 የሚሰጥ ሲሆን፥ ከየካቲት-21 እስከ የካቲት-25 ቀን 2014 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው እንደሚቆዩም ከትምህርት ቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከየካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን የትምህርት ቢሮው የትምህርት ካላንደር ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of text that says 'አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ BIIROO BARNOOTA BULCHINSA MAGAALAA FINFINNEE ADDIS ABABA CITY ADMINISTRATION EDUCATION BUREAU'
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.