Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በወረራቸው የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች በቂ የጤና ክትትል ማግኘት ያለባቸው ዜጎች ለከፋ ችግር ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት አሸባሪ ቡድን በወረራ በያዛቸው የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች በቂ የጤና ክትትል ማግኘት ያለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ለችግር መዳረጋቸውን የዞኑ ጤና መመሪያ አስታውቋል፡፡
 
የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት አያሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷በዞኑ 6 ሆስፒታሎች፣ በርካታ የግል የጤና ተቋማት እና ጤና ጣቢያዎች ለእናቶች የወሊድ አገልግሎት እና ክትትል ይሰጡ ነበር።
 
ይሁን እንጂ አሸባሪው ትህነግ አካባቢዎቹን ከተቆጣጠረ ወዲህ ተቋማቱ ሙሉ በሙሉ በመውደማቸውና ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው እናቶች በዚህ ወቅት ምን እንደገጠማቸው ማወቅ አይቻልም ነው ያሉት፡፡
 
ከወላድ እናቶች በተጨማሪ በዞኑ ውስጥ የተለያዩ መድሃኒቶችን ይወስዱ የነበሩ ሕሙማን ሕክምናቸው በመቋረጡ አሁን ላይ በሕይወት ይኖራሉ ለማለት እንደሚቸገሩ ነው የገለጹት ፡፡
 
በዞኑ ከ18 ሺህ በላይ የስኳር ታካሚዎች፣ ከ20 ሺህ በላይ የጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ተጠቃሚዎች፣ 1 ሺህ 145 የቲቢ ታካሚዎች እንደነበሩም ወይዘሮ ሰላማዊት አስታውሰዋል፡፡
 
በአሁኑ ጊዜ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች በደሴ ከተማ በሚገኙ 14 የመጠለያ ካምፖችና ትምህርት ቤቶች እየኖሩ መሆኑን የገለጹት ሃላፊዋ ÷በእነዚህ ጣቢያዎችም በርካታ ህጻናት፣ ወላድ እና ነፍሰ ጡር እናቶች ይገኛሉ ብለዋል።
 
በይከበር አለሙ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.