Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ከ302 ሺህ ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 302 ሺህ 400 ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች፡፡
 
ድጋፍ የተደረገው ክትባትም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡
 
ክትባቱ በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.