Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መስከረም 20 በሚካሄደው ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በክልሉ የፊታችን መስከረም 20 ቀን በሚካሄደው ምርጫ ዙሪያ እየተወያየ ነው፡፡
 
በውይይቱ በጸጥታ ምክንያት ምርጫ ያልተካሄደባቸው፣በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ የሚደገምባቸውና በፍርድ ቤት ውሳኔ ምርጫ እንዲደገም የተወሰነባቸው 31 የምርጫ ክልሎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡
 
በዚሁ መሰረት ፓርቲዎቹ በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በሚካሄድበት ሁኔታና በቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
 
በክልሉ 21 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጸሃይ ወራሳ የምክር ቤት አባል ፓርቲዎች በምርጫው ዙሪያ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ችግሮች ዙሪያ ተወያይቶ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.