Fana: At a Speed of Life!

ክፉዎች ባለቤቴን በግፍ ገደሉብኝ፤ ልጆቼንም ያለ አባት አስቀሩብኝ – ወ/ሮ ሉባባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትህነግ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በ3 ቀበሌዎች ውስጥ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ከመግደል ባለፈ በመንግስት ተቋማት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንደደረሰ የቤታቸውን በር በኀይል ሰብሮ በመግባት የሰው ልጅ ሆኖ በሰው ልጅ ላይ ሊፈጽመው የማይችል የጭካኔ በትር እንዳሳረፈባቸው ወይዘሮ ሉባባ ዑመር ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ አባላት የወይዘሮ ሉባባን ባለቤት በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኋላም በአካባቢው በሚገኝ አንድ ወንዝ ውስጥ መጣላታቸውን አስረድተዋል።
የሽብር ቡድኑ በቤት ውስጥ የሚገኝን ሽሮ፣ በርበሬ እና ጨው ሳይቀር በመዝረፍ ቤተሰቡን ችግር ላይ መጣሉንም አንስተዋል።
የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ድርጊት አራት ልጆቻቸውን ያለ አባት እንዳስቀረባቸውም ገልጸዋል።
የሟች ወንድም ሁሴን ወራቂ እንዳሉት አሸባሪው ቡድን አካባቢውን ከወረረ ጀምሮ በሴቶች እና ሕጻናት፤ በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ በደል ማድረሱን ተናግረዋል።
ወንድማቸው በአሸባሪው ቡድን በግፍ ተገድሎ ወንዝ ውስጥ ተጥሎ እንደነበርም ጠቅሰዋል።
በአካባቢው የወገን ጦር መግባቱን ተከትሎም አስክሬን አንስተው መቅበር መቻላቸውን ገልጸዋል።
አቶ ሁሴን የዚህ የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ የአማራን ሕዝብ ማጥፋት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በጋራ በመሰለፍ ማስወገድ እንደሚገባው ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.