Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ”ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” የፊርማ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የ”ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግሥት” በሚል መሪ-ቃል በሀገር አቀፍ የተጀመረውን የቅስቀሳ ዘመቻ በክልሉ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
 
አቶ አሻድሊ ሀሰን ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው ዓለም በተለይም ደግሞ ለምዕራባዊያን ለማሳወቅ እና ለማስረዳት ዓላማ ያደረገ መሆኑ አመልክተዋል፤ ዘመቻው የዜግነት ዲፕሎማሲም አካል ነው፡፡
 
በክልሉ በዘመቻው ላይ 50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ወጣቶችን የሚሳተፉበት እና የሀገር ሉዓላዊነት የማስጠበቅ አካል ተደርጎ የሚወሰድ ወሳኝ ተግባር መሆኑን አቶ አሻድሊ ሀሰን አስታውቀዋል፡፡
 
ዘመቻው በዓለም አቀፍ ሚዲያ በበለጸጉ ሀገራት ዘንድ የተፈጠረውን ብዥታ የምናጠራበት እና ለሀገራችን አለኝታነታችንን የምናረጋግጥበት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት ባለፋት 27 ዓመታት ያደረገው የኢኮኖሚ አሻጥር ይባስ ብሎ ገንዘቡን ተጠቅሞ የውጭ ሚዲያዎች በመግዛት የተዛባ መረጃ ለምዕራባውያን ሲያስተላልፍ የነበረውን የሚመክት ዘመቻ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
 
በሀገራችን በአሸባሪ ህወሓት የተከፈተባትን ጦርነት የማሳወቅ፣ መንግሥታችን ለሰላም ያለውን ፅኑ አቋም ለማሳየት እና የውጭ ጫናን በብቃት ለመመከት ታሳቢ ያደረገ ሀገራዊ ዘመቻ እንደሆነም ታውቋል፡፡
 
በዘመቻው በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች የሀገራቸውን መንግሥት ሐቅ ደግፈው እና እውነታውን አውጥተው የምዕራባዊያን መንግሥታትን ለማሳወቅ የሚረባረቡበት እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በዚህ የቅስቀሳ ዘመቻ መላው ዓለም በተለይም ደግሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የኢትዮጵያን እውነታ እንዲረዱ እና የአሸባሪውን ህወሓት እና ተላላኪዎቹን ሴራ እስከምን እንደሆነ ለማሳየት ያለመ ነው፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.