Fana: At a Speed of Life!

አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑን የፌዴራል የስነ-ምግባር እና ጸረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
 
ኮሚሽኑ በ2013 ዓ.ም የሃብት ምዝገባ አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም እቅድን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
 
የኮሚሽኑ የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዳይሬክተር መስፍን በላይነህ፤ በተጠናቀቀው ዓመት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ተመራጮች፣ የመንግስት ተሿሚዎች እና ሰራተኞች ሃብት አስመዝግበዋል።
 
በአመቱ የ705 ሃብት አስመዝጋቢዎች መረጃ ትክክለኛነት መረጋገጡንም ገልጸዋል።
 
በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ፣ በሀረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተሻለ አፈፃፀም እንደነበርም ጠቅሰዋል።
 
በ2014 ዓ.ም በፌዴራልና በሁሉም ክልሎች ሙሉ በሙሉ የሃብት ምዝገባ ይደረጋል ብለዋል ዳይሬክተሩ።
 
አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ የመንግሥት ምስረታ የሚካሄድ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.