Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኬኒያ የድንበር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የኬኒያ መንግስታት የሞያሌ በአንድ ድንበር የሚያልቅ(አንድ አለቅ) የድንበር አገልግሎት ማዕከል የአሰራር ሂደት መመሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጉምሩክ ኮሚሽን እና በኬንያ የድንበር ቁጥጥር እና ስራ ማስተባበሪያ ኮሚቴ ተፈራርመውታል፡፡

የአሰራር ሂደት መመሪያ ስምምነቱ ባሳለፍነዉ ዓመት ሰኔ 1ቀን አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የሞያሌ አንድ -አለቅ የድንበር አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ወደስራ እንደሚያስገባ ተመላክቷል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የድንበር ነክ ጉዳዮችን የሚቆጣጠሩ ተቋማት ሰራተኞች የተቀናጀ የድንበር አስተዳደር ስራዎችን በተሳካ መልኩ መተግበር እንዲችሉ አቅም ይፈጥራል ተብሏል፡፡

ከፊርማ ስነ ስርዓቱ ጎን ለጎንም ሁለቱ ሀገራት በሞያሌ የአንድ- አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከል ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያና ከኬንያ የተወጣጡ የተለያዩ የግሉ ዘርፍ አባላት እና ተቋማት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.