Fana: At a Speed of Life!

በአዳነች አቤቤ የሚመራው ልዑካን ቡድን ሰመራ ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራ የልዑካን ቡድን በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገባ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባሀብቶችን እና የንግዱን ማህበረሰብ ያካተተ ልዑካን አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገብቷል።

ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካኑ አቀባበል ማድረጋቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.