Fana: At a Speed of Life!

በሃዋሳ ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሲጥሩ ለነበሩ አካላት ዕውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሲጥሩ ለነበሩ አካላት የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

አስተዳደሩ የኮቪድ -19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ትልቅ መስዋዕትነትና ተጋድሎ ሲያደርጉ ለነበሩት የህክምና ባለሙያዎች ፣የፅዳት ሰራተኞች ፣አሽከርካሪዎችና የጤና ተቋማት የእዉቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት በዛሬዉ እለት በሀዋሳ አካሄዷል።

በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ በመቀጠል በርከት ያሉ የህክምና ተቋማት የሚገኙባት ሀዋሳ ከተማ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተቋማቱና ባለሙያዎቹ ያደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ ሊያስመሰግናቸዉ ይገባል ያሉት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ናቸዉ።

ምክትል ከንቲባዉ አያይዘዉም÷ ‘’በፈታኝ ወቅት ህይወታችሁን መስዋዕት አድርጋቹህ ለሀገራችሁና ለህዝባቹ በመቆማችሁ ምስጋና ይገባችኋል’’ ብለዋል።

ከሁሉም የመንግስት እና የግል የህክምና ተቋማት የተወጣጡ ባለሞያዎች ናቸዉ የሰርተፍኬት፣ የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸዉ ።
የህክምና ባለሙያዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የእዉቅናና የምስጋና ሽልማቱ የበለጠ ለሀገራቸዉ ሊሰሩ እንዳነሳሳቸዉ ጠቁመዋል።

ያንን ከባድ ጊዜ የህይወት መስዋዕት ጭምር በመሆን እንዳሳለፉትና እጅግ ከባድ ጊዜ እንደነበር ገልጸው÷ አሁንም ሃገራቸዉ በምትፈልጋቸዉ ቦታ ሁሉ ግንባር ቀደም በመሆን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ስላደረገላቸዉ የምስጋና ፕሮግራም አመስግነዉ÷ ህብረተሰቡ አሁንም ከመዘናጋት መቆጠብ እንዳለበት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በብስራት መንግስቱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.