Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ኮሚሽን አመራሮች ከተመድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን አመራሮች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዛሬ በተካሄደው ውይይት ላይ ዶክተር ካትሪን ሶዚ የተመድ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ማስተባበሪያ ኃላፊ እና ቱራን ሳሌ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ ከተመድ የዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በተጣጣመ መንገድ በተሰናዳው የኢትዮጵያ ሃገራዊ የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ትግበራ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

የአስር አመቱን እንዲሁም የዘላቂ የልማት ግቦችን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም፣ በሃገራዊና ክልላዊ ደረጃ በፕላን እና በስታትስቲክስ አቅም፣ በልማት ዕቅድ ክትትልና ግምገማ ሥርዓት እንዲሁም በተቋማዊ አቅም ግንባታ ላይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው የተቀናጁ ድጋፎች ላይ ምክክር ተደርገዋል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ቀደም የተመድ የተለያዩ ተቋማት ለኢትዮጵያ ያደረጉትን ድጋፍ ያስታወሱት ኃላፊዎቹ÷ ለአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ እና የተመድ የዘላቂ የልማት ግቦች 2030 መሳካትም ይኸው ድጋፍ በቀጣይነት ይቀጥላል ተብሏል፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኃላፊ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘርፎች ላይ በተቋም አቅም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመለየት የዳሰሳ ጥናት እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህንኑ የዳሰሳ ጥናት ሲጠናቀቅ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ጋር በመሆን የመካከለኛ ዘመን ሃገራዊ የድጋፍ ማዕቀፍና ዝርዝር ፕሮግራም እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡

ይህ የተቀናጀ ሃገራዊ የድጋፍ ማዕቀፍና ዝርዝር መርሃ ግብር የተመድ ኤጀንሲዎችን ጨምሮ የሁሉንም የልማት አጋሮችን ድጋፍ አንድ ላይ ለማቀናጀት ይረዳል መባሉን ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.