Fana: At a Speed of Life!

የሰው ሰራሽ ኩላሊት የተሳካ ሙከራ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኩላሊት ህመም ችግርን ለመቅረፍ የሚሰራው የኩላሊት ፕሮጀክት ሰው ሰራሽ ኩላሊትን የመጀመሪያ ምርት የተሳካ ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

የኩላሊት ህመምተኞች ከኩላሊት እጥበት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጫናና ስቃይ ውጥ እንደሚገቡ ይታወቃል፡፡

ይህንን ችግር ያስተዋሉ ተመራማሪዎች የኩላሊት ህመምተኞችን ከዚህ ችግር ሊያላቅቅ የሚችል ከፍተኛ ምርምራ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ምርምሩም አድጎ የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ኩላሊት ተሰርቶ የተሳካ ሙከራ እንደተደረገበት መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ሰው ሰራሽ ኩላሊቱ 650 ሺህ የአሜሪካን ዶላረ እንደሚያወጣ የተነገረ ሲሆን÷ ፕሮጀክቱም ኪድኒ ኤክስ በተሰኘ በአሜሪካ የጤናና የአገልግሎት ክፍል እና የአሜሪካ ኔፍሮሎጂ ማህበረሰብ ጥምረት የተሰራ ነው፡፡

ሰው ሰራሽ ኩላሊቱን ሰርቶ ያቀረበው የተመራማሪዎች ቡድን በዚህ ስራው በአለም ውስጥ በዘርፉ ሽልማትን ካገኙ ከስድስት ምርምሮች አንዱ መሆኑን ቴክኖሎጂ ዶት ኦርግን ጠቅሶ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መረጃውን አጋርቷል፡፡

ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የምርምር ቡድኑ በቤት ውስጥ ደምን የሚያጣራ የኩላሊት ስራን ተክቶ ሊሰራ የሚችል መሳሪያን በማቅረብ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሰው ሰራሽ ኩላሊቱንም እነዚህን ሁለት ተግባራት መፈጸም በሚችል መልኩ ሰርቶ አቅርቧል፡፡

እንደ ምርምር ቡድኑ ሀሳብ ከሆነ ሰው ሰራሽ ኩላሊቱ ታካሚዎች በኩላሊት እጥበት ምክንያት ከሚመጣ የስነ-ልቦና ጫና ያላቅቃቸዋል፡፡

መሳሪያው በራሱ በታካሚው የደም ግፊት ብቻ ታግዞ የሚሰራ ሲሆን÷ ምንም አይነት የደም ማቅጠኛም ሆነ ሌላ መድሀኒት እንደማያስፈልገው ታውቋል፡፡

ለኩላሊት ታካሚዎች የሚሰጠው የኩላሊት እጥበትም ሆነ በበጎ ፈቃደኞች የሚለገሱ ኩላሊቶች ንቅለ ተከላ ከፍተኛ የሆነ ተጓዳኝ ችግር የሚያስከትሉ በመሆኑ ይህኛው መንገድ የተሸለ የታካሚዎችን ጤና የመመለስ ብቃት እንዳለው ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.