Fana: At a Speed of Life!

የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እና ቤተሰቦቻቸዉ ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የምግምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉን ያስተባበሩት አቶ ታዲዮስ ጌታቸዉ ይህ ዛሬ የተደረገዉ ድጋፍ ከችግሩ አሳሳቢነት የተነሳ በቂ ነዉ ባይባልም በቀጣይ በደሴ ከተማ ተጠልለዉ ያሉ ተፈናቃዮችን በሁሉም ካምፕ ተደራሽ የሚያደርግ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡
አቶ ሰይድ የሱፍ የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በበኩላቸዉ ÷ ችግሩ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
ይህን ችግር መንግስት ብቻዉን የሚሸፋነዉ ባለመሆኑ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ያደረገዉ ድጋፍ የሚበረታታ ነዉ ብለዋል።
በተጨማሪም ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ትልቅ ጥረት የሚጠይቅ ሲሆን÷ በጉዳዩ ላይ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳየዉ ቸልተኝነት የተዛባና አሳዛኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.