Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት መራዘሙን ዓለም ዓቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ በአውስትራሊያዋ ባትረስት ከተማ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በየካቲት 19/2022 ሊያካሄደው አቅዶት የነበረውን 44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአንድ ዓመት ማራዘሙን ገልጿል፡፡
ሻምፒዮናው የተራዘመበት ምክንያትም አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከለከል ከመላው ዓለም የሚመጡ ጎብኝዎች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ በማውጣቷ ነው ተብሏል፡፡
በዚሁ መሠረት ውድድሩ በአንድ ዓመት ተራዝሞ የካቲት 18/2023 እንደሚካሄድም የዓለም አትሌቲክስ ማሳወቁን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.