Fana: At a Speed of Life!

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ በጋራ የባዮ ጋዝ ግንባታ ለማኅበረሰቡ ለማድረስ የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ ተቋማቱ በጋራ በመሆን በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ምዕራብ ዓባያ፣ ቁጫ፣ ጨንቻና ገረሴ ወረዳ ለሚገኙ ነዋሪዎች የባዮ ጋዝ ግንባታ ለማካሄድ እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለሥራ ማስፈጸሚያ 1 ሚሊየን 875 ሺህ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ÷ የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲም በበኩሉ 4 ሚሊየን 54 ሺህ 115 ብር ድጋፍ ማድረጉን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በውል ስምምነቱ የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ባለሙያዎች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የጋሞ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.