Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል የማስቀመጥ ሥራ በስኬት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት መከናወኑ ተገልጿል፡፡
 
በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች መካከል በዩኒት 10 ላይ የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካል በቦታው ላይ የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል፡፡
 
ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት ያላቸው ሲሆን ÷ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን እንደሚመዝን ተመላክቷል፡፡
 
ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።
 
የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.