Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ ከአሜሪካን አምባሳደር የሰብዓዊ ድጋፍን ማጠናከር ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ኮሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ጋር የሰብዓዊ ድጋፍን ማጠናከርና ማስፋፋት ላይ ተወያይተዋል።

የውይይቱ አላማ የህውሓት የጥፋት ቡድን ባደረሰው ጥቃት በአማራ እና አፋር ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ በአፋጣኝ ለማዳረስ እና የመልሶ ማቋቋም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስልቶችን ለማጠናከር ነው።

ሚኒስትሯ በመንግስት በኩል በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ከሚገኙ ዜጎች በተጨማሪ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች ከቀዬአቸው ርቀው የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ለዚህም የሰብዓዊ አጋሮች ድጋፍ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አመልክተዋል።

አምባሳደር ፓሲ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚከታተሉ መሆኑን ገልጸው÷ የአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ ለረጅም ዘመናት የቆየውን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

እየተደረገ ያለው የሰበዓዊ ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዳይሬክተር ሾን ጆንስ በበኩላቸው÷ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በአማራ እና አፋር ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ያለውን ሰብዓዊ ርብርብ እያገዘ መሆኑንና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አካባቢዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ድጋፉ በስፋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.