Fana: At a Speed of Life!

“ነፍሳችን እስካለች ራሳችንንም ሀገራችንንም አናስነካም” የአምቦዎቹ እህትማማቾች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትውልድ ስፍራቸው አምቦ ነው፤ እህትማማቾቹ ብርቆ ተሾመ እና ጫልቱ ተሾመ።

የቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ካስመረቃቸው ምልምል ወታደሮች ናቸው።

የትውልድ ስፍራቸው አምቦ ቢሆንም የሚኖሩት ግን ለገጣፎ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ስትጣራ እኛ ሴቶች ነን ቆይ ወንዶቹ ይዝመቱ ሳይሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ተቀላቀሉ፡፡ አምቦ ያሉት እናትና አባት ዜናውን የሰሙት ዘግይተው ነው፡፡

ስልጠናቸውን በብቃት ተወጥተው በመሰረታዊ ውትድርና ምልምል ወታደሮች ሆነው  ተመርቀዋል፡፡

ስለስልጠናው ጠይቀናቸው “ምንም አልከበደንም ፡፡ ሰው የሚሰራውን ሰርተናል” በማለት በኩራት መልሰውልናል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ ስላላቸው ዝግጁነት ሲያስረዱም “ነፍሳችን እስካለች ራሳችንንም ሀገራችንንም አናስነካም፤ እናሸንፋለን”  ሲሉ መመለሳቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.