Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ እስከአሁን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶዝ በላይ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ አድርጋለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)እንግሊዝ ለኢትዮጵያ እስከአሁን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶዝ በላይ የአስትራዜኒካ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ድጋፍ ማድረጓ ተገለፀ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ÷በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ተወካይ አሌክስ ካሜሮን እና የእናቶችና ህፃናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም የኮተቤ ጤና ጣቢያ በኮቪድ -19 ክትባት ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በተመለከተ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ÷ የእንግሊዝ መንግስት በኮቫክስ የክትባቶች ጥምረት በኩል እስካሁን ለኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶዝ በላይ የአስትራዜኒካ ክትባት ድጋፍ መደረጓን የገለፁ ሲሆን÷ ለድጋፉ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ተወካይ አሌክስ ካሜሮን በበኩላቸው÷ የእንግሊዝ መንግስት በኮቫክስ የክትባቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽ ለማድረግ ለጥምረቱ አባል አገሮች 20 በመቶ ዜጎች ክትባት የማዳረስ እቅድ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ በጉብኝቱ ባዩት ነገር ደስተኛ እንደሆኑ እና በቀጣይም በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት የአስትራዜኒካ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.