Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ግብዓት ድጋፍ አደረገ።
በኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት ድጋፉን በሃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም አትሌት ሃይሌ አበርክቷል።
ለተፈናቃዮቹ የተደረገው ድጋፍም 500 ኩንታል ዱቄት እና 2 ሺህ 500 ሊትር ዘይት ነው።
በተጨማሪም አትሌቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ አሸባሪ ቡድኑ በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።
የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ሃይል አትሌት ሻለቃ ሃይለገብረ ስላሴ በአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን በዳስ ለሚማሩ ህጻናት ያስገነባውን ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ማውደማቸው ይታወቃል።
አትሌቱ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ በተፈጸመው ድርጊት እጅግ ማዘኑን የገለጸ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን ማውደም በጦር ወንጀለኝነት መታየት እንዳለበትም ጠይቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.