Fana: At a Speed of Life!

የመገናኛ ብዙኃን ስራ አስፈፃሚዎች በትህነግ ጉዳት የደረሰበትን የደቡብ ጎንደር ዞን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ስራ አስፈፃሚዎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰበትን የደቡብ ጎንደር ዞን ጉብኝተዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ባደረሰው ጥቃት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን፣ የግለሰብ ሀብቶችን እና የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከትናንት ጀምሮ ጎብኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ስራ አስፈፃሚዎች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት ተወካዮች የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በጉብኝቱ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ መልሶ ለመገንባት መገናኛ ብዙኃኑ በውል ተገንዝበው ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ማድረስ ይገባቸዋል ተብሏል፡፡
በጉብኝቱ የደቡብ ጎንደር ዞን ህዝብ በተለይም የደብረታቦር ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ እና በህልውና ዘመቻ እየተሳተፉ ለሚገኙ ወገኖች እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.