Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ቢሾላ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ምልምል ወታደሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽ ቢሾላ መሠረታዊ የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ምልምል ወታደሮችን  አስመርቋል፡፡

ሰልጣኞች መሠረታዊ የውትድርና ስልጠናን በአምስት የስልጠና አይነቶች በማዕከሉ  መውሰዳቸው ተገልፃል፡፡

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች  ተገኝተዋል።

ሰልጣኞች በወሰዱት አጠቃላይ ስልጠና የተቀመጡላቸውን ግብ ማሳካታቸውን የአዋሽ ቢሾላ መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሀላፊ ኮ/ር ተረፈ ጩሪሶ ገልፀዋል ፡፡

ተመራቂዎቹም ህዝባዊ አደራቸውን በጀግንነት ወኔ ለመወጣት ያላቸውን ዝግጁነት አንስተዋል፡፡

የምድር ሀይል ምክትል አዛዥ  የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን፥ የህወሓት አሸባሪ ቡድንን ማጥፋት በታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል።

ምልምል ወታደሮቹ የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ስልጠናውን በብቃት በማጠናቀቃቸው እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል፡፡

 

በሜሮን ሙሉጌታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.