Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ ከሰሜን ወሎ ግምባር ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ በሰሜን ወሎ ግምባር ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያዩ።

በግምባሩ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ለምንም የማይበገረው የመከላከያ ሠራዊቱ ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን አድንቀዋል።

ጄነራል አበባው በውይይቱ ሠራዊቱ በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ሀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ÷ ሰራዊቱ ህዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ሀይል አንገት እያስደፋ ሰርጎ የገባባቸውን አንዳንድ ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በህዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማህበረሰብ ወደ ቀዬው እንዲመለስ ለማድረግ ግምባር ላይ ያለው ሀይል የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ተቋሙም በአሁኑ ጊዜ ብቁ ሠራዊትን በማፍራት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.