Fana: At a Speed of Life!

የቡና አመራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና አምራች አርሶ አደሮችን ፍትሐዊና ተጠቃሚ የሚያደርግ “የአፍሪካ ተጠቃሚነት ድርጅት ፎረም 2021” በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ተካሄደ፡፡

በፎረሙ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አምባሰደር ምስጋኑ አርጋ÷ ቡና የአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ 25 በመቶ በማስገኘት ለኢትዮጵያ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባሻገር ለ26 ሚሊየን ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የስራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመዋል ፡፡

አምባሳደሩ ቡናን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ያስተዋወቀችው ኢትዮጵያ በዋጋ ደረጃ ፍትሐዊ ተጠቃሚ አለመሆኗ ከሚታዩ ችግሮች መካከል የግብይቱ ሰንሰለት መንዛዛት እና እሴት ሳይጨመር መላኩ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡

እንደነዚህ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ቀጣይነት ያለው አቅርቦት ፣ ምቹ የአየር ንብረት እና በውጭ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ያስፈልገናል በማለት አሳስበዋል፡፡

ለ15 ዓመታት ይህን ኢኒሼቲቭ እውን እንዲሆን ሲሰሩ የነበሩት ጥበቡ አሰፋ በበኩላቸው÷ አፍሪካ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግኑኝነት ከልመና ነፃ የሆነ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ታስቦ የተጀመረ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

በፎረሙ የግብርና ሚኒስቴር፣ የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ፣የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ፣ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ አብዝሀ ህይወት ኢንሲቲትዩት፣ የኢትዮጵያ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ፣በውጭ የሚኖሩ አፍሪካዊያኖች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የቀድሞ የአሜሪካ ሴነት እና ኮንግረስ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ በሶስት የአሜሪካ ግዛቶች እንደሚጀምርም መገለፁን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.