Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችሁ ነው – ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት የሽብር ቡድን በግፍ የተገደሉት የለቅሶ ስነ ስርዓት በነፋስ መውጫ ከተማ ተከናወነ፡፡

የሽብር ቡድኑ በደቡብ ጎንደር በቆየባቸው ጊዜያት በርካታ ንፁሃንን በግፍ ከገደለ በኋላ ቀብራቸው እንዳይፈፀም እና የሟች ቤተሰቦች እንዳያለቅሱ በመከልከል ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈፅሟል።

ዛሬ በጋይንት የተለያዩ አካባቢዎች በግፍ የተገደሉ ዘመድ አዝማድ ተሰባስበው የለቅሶ ስነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

ከመገናኛ ብዙሃን ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው ልዑኩ የሟች ቤተሰቦችን አፅናንቷል።

በጉብኝቱ የተገኙት ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት÷ ‘‘አብዛኞቹ ሟቾች ወጣት ናቸው፤ ለኛ ሲሉ ተሰውተዋል፤ ሟቾቹ ዘላለም ሲዘከሩ ይኖራሉ’’ ብለዋል።

‘’እናንተም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችሁ ነው፤ የሽብር ቡድኑ የንፁሀንን ደም አፍሶ አይቀርም’’ ብለዋል።

በለቅሶ ስነ ስርዓቱ ከአንድ ቤተሰብ እሰከ አራት ወንድማማቾች የሞቱባቸው እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.