Fana: At a Speed of Life!

“የእኛ ዝግጅት ለጁንታዉ ሳይሆን ለጋላቢዎቻቸዉ ነዉ ” ሌ/ ጀ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ” የእኛ ዝግጅት ቀድሞም ለተሸነፈው ለጁንታዉ ቡድን ሳይሆን ለጋላቢዎቻቸዉ ነዉ ” ሲሉ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀነራል ባጫ ዛሬ በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተዉ ለተመራቂዎች መልእክት አስተላልፈዋለ።
በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ሀገራችን ኢትዮጲያን ፈተና ሲያጋጥማት የመጀመሪያዋ አይደለም ያሉት ጀኔራል ባጫ ያሁኑን ፈተና ለየት የሚያደርገዉ በሀገር ሀብት ሰልጥነዉ፣ በሀገር ሀብት ኖረዉ የራሳቸዉን ጦር ለመዉጋት የመጀመሪያዎቹ የውስጥ ጠላት መሆናቸው ነዉ ብለዋል።
ጀነራል መኮንኑ አያይዘዉም በ1888 ዓ.ም በዓድዋ ጦርነት ወቅት ለፋሽስቱ ሃይል ይሰሩ የነበሩ ባንዳዎች እንደነበሩ አንስተዉ፥ በወቅቱ የነበሩት ጀግኖች ወጣቶችና ታማኝ ኢትዮጵየውያን በከፈሉት መስዋዕትነት ወራሪዉ የጣሊያ ጦርና ጀሌዎቹ ድባቅ መመታታቸውን አስረድተዋል።
ሌተናል ጀነራል ባጫ ቀጥለውም በ1928 በኢጣሊያ ፋሽስቶች ዳግመኛ ወረራ ሲካሄድብን እጅግ በርካታ የሀገር ተወላጅ ባንዳዎች ቢኖሩም በብዙሀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የተባበረ ክንድ ዋጋቸዉን ቀምሰዋል ተሸንፈዋል ብለዋል።
ጅኔራል ባጫ እንዳሉት በ1969ዓ.ም የዚያድ ባሬ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ባካሄደበት ወቅት የዛሬዉ ጁንታ ህወሃት ኢትዮጲያና ህዝቦቿን መጠበቅ ሲገባዉ ከሶማሊያ ጦር ጎን ተሰልፎ ነበር።
ነገር ግን ከ300 ሺህ በላይ ምልምል ወጣቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልጠና ወስደው በሜካናይዝድና በዘመናዊ መሳሪያ የተደራጀዉን ወራሪዉን ጦር ከነ ባንዳዉ ማክሸፋቸዉ ታሪክ የማይረሳዉ ድል ነዉ ብለዋል።
የዛሬ ተመራቂዎችም የዚህ ተዉልድ የመከላከያ ጋሻዎች በመሆናችሁ ጥሪ ሲደረግላችሁ እናት አባቴ ሳትሉ ለሀገራችሁ በመቆማችሁ ክብርና ሞገስ ይገባችኋል ብለዋል።
“ዛሬ የገጠሙን ጠላቶች ድሮም ከዚያድ ባሬ ጋር የወገኑት ጁንታዎች ናቸዉ። የእኛ ዝግጅት ለጁንታዉ አይደለም፤ ጁንታዉ ቀድሞዉንም ተሸንፏል፤ ዝግጅታችን ለገላቢዎቻቸዉ ነዉ” ብለዋል።
በአንድ ድንጋይ የወረደ ጁንታ ጠመንጃ ታጥቄያለሁ ብሎ ስልጣን ሊይዝ አይችልም ያሉት ጀኔራል ባጫ፥ “ እነሱ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሰይጣንም ጋር እንሰራለን ብለዋል፤ ነገር ግን ኢትዮጵያን ሊያፈሱ አይችሉም፣ ምክኒያቱም እነሱ የሚዋጉት ከ110 ሚሊየን ህዝብ ጋር ነዉና” ሲሉ ተናግረዋል ።
በብስራት መንግስቱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of one or more people, people standing, military uniform and outdoors
14,850
People Reached
1,605
Engagements
Boost Post
1K
68 Comments
50 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.