Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ባለሙያዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
በኬንያ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያዊ ባለሙያዎች ማህበር ለዘላቂ ልማት በተለያዩ የትዮጵያ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 21 ሺህ 897 የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን ማህበሩን በመወከል ዶክተር ታዬ ተፈሪ በኬንያ ለኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ አስረክበዋል።
አምባሳደር መለስ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ ኤምባሲው ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ እየሰራ መሆኑንና ሁሉም በዚህ ወቅት ከአገሩ ጎን መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ሲል ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታና የኮሮና መከላከል ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን ኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.